የግላዊነት ፖሊሲ
ኤማን በገና ማሰልጠኛ — ድረ-ገጽ እና የAndroid መተግበሪያ · Last updated: October 2026
የምንሰበስበው መረጃ
- የመለያ መረጃ፦ ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ ኢሜይል (አማራጭ)፣ የይለፍ ቃል (ተመስጥሮ ይቀመጣል)።
- የተማሪ መረጃ፦ በምዝገባ ጊዜ የሚሰጡ መረጃዎች (ክርስትና ስም፣ አጥቢያ፣ ፎቶ)፣ የትምህርት እድገት፣ ውጤቶች፣ ክትትል (attendance) እና የምስክር ወረቀቶች።
- የሚሰቅሏቸው ፋይሎች፦ የክፍያ ደረሰኝ ፎቶዎች፣ የመዝሙር/የትምህርት ቅጂዎች።
- የመሣሪያ መረጃ፦ የመሣሪያ ስም (ኮርሱ በስንት መሣሪያ እንደተከፈተ ለመቁጠር) እና የማሳወቂያ (push) መለያ።
- የትዕዛዝ እና የጥያቄ መረጃ፦ ከገበያ ቦታው የሚያዝዟቸው ዕቃዎች እና የሚልኳቸው ጥያቄዎች።
መረጃውን ለምን እንጠቀማለን
- ትምህርቱን ለመስጠት፣ ክፍያን ለማረጋገጥ፣ ትዕዛዞችን ለማድረስ እና ጥያቄዎችን ለመመለስ።
- ስለ ትምህርት፣ መልዕክት እና ዝግጅት ማሳወቂያ ለመላክ (በስልኩ ቅንብር ማጥፋት ይቻላል)።
- መረጃዎን አንሸጥም፣ ለማስታወቂያም አንጠቀምበትም።
መረጃውን የሚያስተናግዱ አገልግሎቶች
- Supabase — የመረጃ ቋት እና ፋይል ማከማቻ
- Cloudflare — ድረ-ገጹ እና ሰርቨሩ
- OneSignal (እና Google Firebase) — ማሳወቂያዎች
- YouTube — የትምህርት ቪዲዮዎች
- Google Gemini — በመተግበሪያው ውስጥ ያለው የAI ረዳት እና የቋንቋ ትርጉም። ለረዳቱ የሚጽፉት ጥያቄ ለመመለስ ወደ Gemini ይላካል፤ የይለፍ ቃል ወይም የክፍያ መረጃ አይላክም። የAI መልስ ሊሳሳት ይችላል፤ ተገቢ ያልሆነ መልስ በመተግበሪያው ውስጥ ሪፖርት ማድረግ ይቻላል።
መረጃው ወደነዚህ አገልግሎቶች የሚላከው በተመሰጠረ (HTTPS) ግንኙነት ነው።
መረጃዎን ማየት፣ ማስተካከል እና ማሰረዝ
መለያዎ እና መረጃዎ እንዲሰረዝ በመተግበሪያው ውስጥ «መለያዬ ይሰረዝልኝ» ይጫኑ፣ ወይም ይህን ገጽ ይጠቀሙ፦ መለያ ማሰረዝ። ትምህርት ቤቱ ስልክዎን አረጋግጦ በ30 ቀን ውስጥ ይሰርዛል። በህግ መቀመጥ ያለባቸው የክፍያ መዛግብት ብቻ ለተወሰነ ጊዜ ይቆያሉ።
ልጆች
ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎች መረጃ የሚመዘገበው በወላጅ ወይም በአሳዳጊ ፈቃድ ነው።
ለውጦች
ይህ ፖሊሲ ሲቀየር በዚህ ገጽ ላይ ይታተማል።
In English (summary)
Eman Begena collects the account details you give (name, phone, optional email), student records (progress, attendance, results, certificates), files you upload (payment receipts, recordings), a device name and a push-notification id. We use them only to teach, confirm payments, deliver orders, answer questions and send notifications. We do not sell your data or use it for advertising. Data is processed by Supabase, Cloudflare, OneSignal/Firebase, YouTube and Google Gemini (the in-app AI assistant and translation; only the question you type is sent) over encrypted connections. Inappropriate chat messages and AI answers can be reported inside the app. To delete your account and data, tap «መለያዬ ይሰረዝልኝ» in the app or use this page; the school deletes it within 30 days, keeping only payment records the law requires.